በዚህ ዓመት መጨረሻ 30 ሚልየን ኢትዮጵያውያንን ለብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ ታቅዷል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበዚህ ዓመት መጨረሻ 30 ሚልየን ኢትዮጵያውያንን ለብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ ታቅዷል
በዚህ ዓመት መጨረሻ 30 ሚልየን ኢትዮጵያውያንን ለብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ ታቅዷል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.05.2025
ሰብስክራይብ

በዚህ ዓመት መጨረሻ 30 ሚልየን ኢትዮጵያውያንን ለብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ ታቅዷል

የ 'ፋይዳ' ዲጂታል መታወቂያ ሶፍትዌር መሀንዲስ የሆኑት ኤልሮይ ታደለ እስካሁን 15 ሚሊዮን ሰዎች ለዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“ፋይዳ ከተለያዩ ስርዓቶች ጋር ይሠራል፡፡ በሀገሪቱ ከሁሉም የአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በሚባል ደረጃ ተዋህደናል” ብለዋል፡፡

አክለውም ተቀባይነቱ እንደተጠበቀው ባይሆንም አሁን ላይ እየሰፋ መምጣቱን ገልፀው የመመዝገቢያ መሳሪዎችን ከውጭ በማስገባት ረገድ የነበሩ ተግዳሮቶች ከባድ እንደነበሩ አመልክተዋል።

“ሰዎች አሁን ከመጠራጠር ይልቅ በጥሩ ጎኑ እያዩት ነው፡፡ በተለያዩ ማሕበራዊ ትስስር ገጾች በኩል እየደረስን በመሆኑ የአጠቃቀም ደርጃው በሂደት እየጨመረ ነው፡፡ በግልም እየሄድን የምክክር ስብሰባዎችን እናካሂዳለን”

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሔራዊ መታወቂያ አማካኝነት የ9 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር የዲጂታል ልውውጥ መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡

የመታወቂያ ስርዓቱ በጤና፣ ፋይናንስ እና ትምህርት ዘርፎች እንደተዋሃደም በአይዲ ፎር አፍሪካ 2025 ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልጸዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0