የብዝሃ ሕይወት መመናመንን ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ
12:41 21.05.2025 (የተሻሻለ: 13:04 21.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የብዝሃ ሕይወት መመናመንን ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ
የዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን ከግንቦት 12 እስከ 16 ድረስ “ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዓለም አቀፉን የብዝሃ ሕይወት ስምምነት ማንበር፣ ዘላቂ አጠቃቀም እና ጥቅም ተጋሪነት የበዓሉ ትኩረቶች እንደሆኑ በኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግኑኝነት እና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ በፍቃዱ ከፈለኝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ቀኑን በማስመልከት ኤግዚቢሽን የከፈተ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X