ኢትዮጵያ ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሥነ-ምህዳር እንደተሰጣት የግብርና ሚኒስትሩ ተናገሩ
12:02 21.05.2025 (የተሻሻለ: 13:24 21.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሥነ-ምህዳር እንደተሰጣት የግብርና ሚኒስትሩ ተናገሩ
ጅማ ከተማ በትናትናው እለት ተከብሮ የዋለውን ሁለተኛውን የዓለም የንብ ቀን አስተናግዳለች፡፡
ኢትዮጵያ በንብ ምርት ያደረገቻቸው ለውጦች ታይተው ቀኑን እንድታከብር መመረጧን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ቀደም ብለው አስታውቀዋል።
ሀገሪቱ ቀኑን ለማክበር በመመረጧ ደስተኛ እንደሆነች እና ለዘርፉ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖርው ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊየን በላይ ህብረ ንብ እንዳላትም ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ የንብ ቀን እና 2ኛው የንብ ሀብት ልማት ፎረም እስከ ግንቦት 14 ድረስ በተለያዩ ሁነቶች በጅማ ከተማ ይካሄዳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
