ህንድ በብሪክስ ባንክ እና በእስያ ልማት ባንክ በኩል ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች
13:50 20.05.2025 (የተሻሻለ: 14:34 20.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ህንድ በብሪክስ ባንክ እና በእስያ ልማት ባንክ በኩል ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች
ህንድ በተቋማቱ ውስጥ ያላትን ተጽዕኖ በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት ሲሉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር አኒል ኩማር በ3ኛው "ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2025” ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ተናግረዋል።
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ህንድ ወሳኝ ሚና መጫወቷንም አንስተዋል ሲል የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።
“ኢትዮጵያ ባላፈው ዓመት የብሪክስ አባል ከሆነች በኋላ ተጽዕኖዋ የጨመረ ሀገር ሆናለች፡፡ ጆሃንስበርግ በተካሄደው ጉባኤ ህንድ ነበረች ሃሳቡን በኩራት ያቀረበችው” ብለዋል፡፡
ይህም ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግኑኝነት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ ሁለቱ ሀገራት በብሪክስ ማዕቀፍ ትብብራቸውን እንዲያሳድጉ መንገድ ከፍቷል ሲሉ ተናግረዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X