ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ትልቁን ሕንጻ ልትገነባ ነው
12:38 20.05.2025 (የተሻሻለ: 12:54 20.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ትልቁን ሕንጻ ልትገነባ ነው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያስገነባዋል የተባለው የዋና ምሥሪያ ቤት ሕንጻ 197 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ስፋት፣ 327.5 ሜትር ርዝመት እና 62 ፎቅ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
በዚህም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ትልቁን ሕንፃ የንግድ ባንክን የ209.7 ሜትር እና የ53 ወለል ሕንጻ የሚበልጥ ይሆናል፡፡
ከሜክሲኮ አደባባይ አቅራቢያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሊገነባ የታቀደው ሕንጻ 445 ሚልየን ዶላር ያወጣል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ በገንዘብ እና በሎጂስቲክስ ችግሮች ምክንያት ቆሞ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁን ለግንባታው ጨረታ እንዳወጣ ተሰምቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X