የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል

ሰብስክራይብ

የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል

የፕሬዝዳቱ ፅህፈት ቤት "የጉብኝቱ ዓላማ በአሜሪካና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ዳግም ማስተካከል እና ማነቃቃት ነው" ብሏል።

ጉብኝቱ በዋናነት የሁለትዮሽ፣ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነቶችን እንደገና ማነፅ ላይ ያተኩራል።

አሜሪካ በአፍሪካነሮች (ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን) ላይ ያነጣጠሩ የመሬት ወረራዎች ዙሪያ ባቀረበችው ክስ ምክንያት በአሜሪካ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቷል። ትራምፕ "በዘር ላይ የተመሰረተ መድልዎ" ሰለባዎች ናቸው በማለት የአፍሪካነር "ስደተኞችን" አሜሪካ ውስጥ ለማስፈር በየካቲት ወር ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ባለፈው ሰኞ የመጀመሪያው ቡድን አሜሪካ ደርሷል።

ፕሪቶሪያ ክሱን መሠረተ ቢስ እና ፖለቲካዊ ያለችው ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ምንም ዓይነት የዘር መድልዎ የለም ብላ ተከራክራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0