"የአፍሪካ ቡድን የዓለም ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት ተስፋ አለኝ፤ ለዚያ የሚሆን እምቅ ችሎታ አለ" ሲል የቀድሞ የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ተናገረ

ሰብስክራይብ
"የአፍሪካ ቡድን የዓለም ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት ተስፋ አለኝ፤ ለዚያ የሚሆን እምቅ ችሎታ አለ" ሲል የቀድሞ የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ተናገረ

ጄሬሚ ንጂታፕ ሲኤስኬ ሞስኮ ዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ያነሳበትን የ20ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ የተገኙ "በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች እንደተደሰቱ" ተስፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

“ወደ ሞስኮ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ውብ ከተማ ናት" ያለው የቀድሞው የካሜሩን ተጫዋች "ግብዣው በደረሰኝ ጊዜ ምንም አላመነታሁም" ሲል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።

የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና የቼልሲ ኮከብ የአፍሪካ ቡድን አንድ ቀን የዓለም ዋንጫን ሲያነሳ ለማየት ተስፋ ያደርጋል።

"ያ ትልቅ መልዕክት ያስተላልፋል። ሞሮኮ ባለፈው የዓለም ዋንጫ ያሳየችው ብቃት በጣም ጠንካራ ነበር። ዓለም አስተውሏል። ይህ ካፍ በድርጅቱ እና በመሠረተ ልማት ልማት ላይ መሥራቱን መቀጠል እንዳለበት ያመለከተ አጋጣሚ ነው" ሲል አጽናኦት ሰጥቶ ተናግሯል።

ወጣት አፍሪካውያን የእግር ኳስ ተጫዋቾች ስኬታማ መሆን ከፈለጉ ጠንክርው መሥራት እና መማር ይጠበቅባቸዋል ሲልም ምክሩን ለግሷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአፍሪካ ቡድን የዓለም ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት ተስፋ አለኝ፤ ለዚያ የሚሆን እምቅ ችሎታ አለ ሲል የቀድሞ የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ተናገረ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአፍሪካ ቡድን የዓለም ዋንጫ ሲያነሳ ለማየት ተስፋ አለኝ፤ ለዚያ የሚሆን እምቅ ችሎታ አለ ሲል የቀድሞ የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋች ተናገረ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0