በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ከ300 በላይ ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ሊገነቡ ነው
11:28 19.05.2025 (የተሻሻለ: 11:44 19.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ከ300 በላይ ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ሊገነቡ ነው
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ግንባታዎቹ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ 126 ወረዳዎች እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡
በገጠር አካባቢዎች ያለውን የመንገድ ተደራሽነትና የትስስር ችግር ለመቅረፍ በ407 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚኒስቴሩ ዴኤታ የትምጌታ አስራት ለሀገር ወስጥ ጋዜጣ ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ ከሰባት ሺህ በላይ የገጠር መንገዶች ግንባታ እንዲሁም ከ10 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የገጠር መንገድ ጥገና አካቷል ብለዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X