ሴኔጋል እና ቡርኪና ፋሶ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ትብብር ፈጠሩ
16:57 18.05.2025 (የተሻሻለ: 17:14 18.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሴኔጋል እና ቡርኪና ፋሶ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ትብብር ፈጠሩ
የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማን ሶንኮ በዋጋዱጉ ጉብኝታቸው ወቅት ሁለቱ ሀገራት መረጃን በተሻለ ሁኔታ እንዲለዋወጡ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በትብብር በመሥራት
▪ የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች መስፋፋትን፣
▪ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን፣
▪ አደገኛ ዝውውሮችን ለመወጋት ቃል ገብተዋል።
መሪዎቹ የሽብርተኝነት እና የአክራሪነት ስጋትን ለመጋፈጥ "የተቀናጀ እርምጃ እንደሚያስፈልግ እና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሀገራዊ ጥረቶችን ሊደግፍ እንደሚገባ" ተናግረዋል።
ሶንኮ ቡርኪና ፋሶ ሽብርተኝነት ላይ በከፈተችው ጦርነት ሴኔጋል ፅኑ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
