በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ቅንጡ የከተማ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በሚቀጥሉት ሰባት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተባለ
13:51 18.05.2025 (የተሻሻለ: 14:14 18.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ቅንጡ የከተማ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በሚቀጥሉት ሰባት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተባለ
በአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፕሮጀክት መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ አምስት ድርጅቶች ከቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር ተፈራርመዋል።
በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገነባው ግዙፍ እና ቅንጡ ሰፈር አካል ለመሆን አምስት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶች ናቸው ተስማምተዋል የተባለው።
35 ሄክታር መሬት ይሸፍናል የተባለው ይህ ፕሮጀክት የንግድ እና ዘመናዊ ህንፃዎች፣ ቢሮዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን እና ሌሎችንም ያካትታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፕሮጀክት ማስጀመሪያ በ2016 ዓ.ም ነሃሴ ወር የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X