ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአፍሪካ ልማት ሀገር በቀል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲዳብር ጥሪ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአፍሪካ ልማት ሀገር በቀል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲዳብር ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአፍሪካ ልማት ሀገር በቀል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲዳብር ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.05.2025
ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአፍሪካ ልማት ሀገር በቀል የሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲዳብር ጥሪ አቀረቡ

መሪው ይህን ያሉት በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

የዳታ ሉዓላዊነት እንደ አህጉር የቴክኖሎጂ ነፃነታችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በትብብር መሥራት አስፈላጊ እንደሆነም አንስተዋል።

"አፍሪካ አጋዥ የሆኑ ፖሊሲዎችን እና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይልን በማቀናጀት ችግሮቿን መፍታት ይገባታል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ ያካበተችውን ልምድ ለማጋራት እና በአፍሪካ ትብብርን ለማጠናከር ቁርጠኛ ነች ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ዛሬ ያበቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0