ቡርኪና ፋሶ የጀግናዋን የቶማስ ሳንካራን መካነ መቃብር አስመረቀች
10:07 18.05.2025 (የተሻሻለ: 10:24 18.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ የጀግናዋን የቶማስ ሳንካራን መካነ መቃብር አስመረቀች
እ.ኤ.አ በ1987 ለተገደሉት ፕሬዝዳንት ሳንካራ እና 12 ባልደረቦቻቸው መታሰቢያ የዋለው ይህ የመካነ መቃብር ህንፃ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ በተገደሉበት ቦታ ላይ ተገንብቷል።
🟠 መቃብሩ ዘመናዊ ሥነ ሕንፃን እና የአካባቢውን የእጅ ጥበብ ያጣመረ ነው።
🟠 የሳንካራን ነፃ፣ የተከበረች እና ጠንካራ ቡርኪና ፋሶን የማየት ህልም ያመለክታል።
🟠 በ20 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ቦታ ሙዚየም፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የኤግዚቢሽን አዳራሽ እና ሌሎች መገልገያዎችን አካቷል።
🟠 87 ሜትር ከፍታ ያለው ማማ በሶስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።
መካነ መቃብሩ ከአምስት በፊት የተመረቀው የቶማስ ሳንካራ መታሰቢያ አካል ነው።
የምረቃው ቀን ግንቦት 9 ቀን 1975 ዓ.ም የቶማስ ሳንካራን መታሰር ተከትሎ ከተነሳው የዴሞክራሲያዊ እና የሕዝባዊ አብዮት ጋር የተያያዘ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X