ሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል ለድርድር መቀመጣቸው ለዓለም ሰላም መልካም ተስፋ ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ተናገሩ
19:49 17.05.2025 (የተሻሻለ: 20:04 17.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል ለድርድር መቀመጣቸው ለዓለም ሰላም መልካም ተስፋ ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ዩክሬን በኢስታንቡል ለድርድር መቀመጣቸው ለዓለም ሰላም መልካም ተስፋ ነው ሲሉ ኢትዮጵያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ተናገሩ
ድርድሩ ጥሩ የሰላም ጅምር ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት የጥናትና ምርምር መሪ የሆኑት ዳርእስከዳር ታዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አክለውም ዘላቂ ሰላም የግጭቱን ዋና መንስዔዎች መፍታት እንደሚሻ ጠቁመዋል።
"ለሩሲያውያን የግጭቱ ዋና መንስዔ የኔቶ ወደ ምስራቅ አውሮፓ መስፋፋት ነው። ሌላው ደግሞ ዩክሬን ሩሲያኛ ተናጋሪዎች ላይ የምታደርሰው በደል ነው" ብለዋል።
ተመራማሪው አውሮፓውያን ግጭቱ እየሄደ ባለበት መንገድ ደስተኛ እንዳልሆኑ፣ ዩክሬን እንድታሸንፍ እና ሩሲያን ድል ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልፀው፤ ይህ የማይሆን ነው ብለዋል።
በአውሮፓውያን እና በአሜሪካውያን መካከል የተፈጠረው ወቅታዊ ልዩነት አሜሪካ ሰላምን እንድትመርጥ፤ አውሮፓ ግን ግጭቱ ይቀጥል የሚል አቋም እንድትይዝ ያደረገ ይመስላልም ብለዋል።
ይህ ክፍፍል መቀጠሉ ላይ ጥሪጣሪያቸውን የገለፁት ተመራማሪው፤ አውሮፓውያን ተቀበሉትም አልተቀበሉትም ሩሲያ እና ዩክሬን ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X