የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ኢስታንቡል በተካሄደው ድርድር ዙሪያ በስልክ ተወያዩ
16:10 17.05.2025 (የተሻሻለ: 16:34 17.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ኢስታንቡል በተካሄደው ድርድር ዙሪያ በስልክ ተወያዩ
ማርኮ ሩቢዮ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመቀጠል ዋሽንግተን ዝግጁ እንደሆነች አረጋግጠዋል ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም የጦር እስረኞችን መለዋወጥ እና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ማዘጋጀት ላይ የተደረጉ ስምምነቶችን በበጎው እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።
ሰርጌ ላቭሮቭ ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር ተባብራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በሩሲያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ስለሚኖረው ቀጣይ ግንኙነት ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
የስልክ ውይይቱ የተካሄደው በአሜሪካ አነሳሽነት ነው
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X