የትራምፕ አስተዳደር አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ ሊቢያ ለማዛወር እቅድ እንዳለው ዘገባዎች አመላከቱ
13:34 17.05.2025 (የተሻሻለ: 13:54 17.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የትራምፕ አስተዳደር አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ ሊቢያ ለማዛወር እቅድ እንዳለው ዘገባዎች አመላከቱ
የትራምፕ አስተዳደር እቅዱን ከሊቢያ አመራሮች ጋር ከወዲሁ መወያየቱን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሁለት ሰዎች እና አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
በሰፈራው ምትክ ዋሽንግተን ከዚህ በፊት ያገደችውን የሰሜን አፍሪካዊቷን ሀገር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ትለቃለች ብሏል ዘገባው።
ይሁን እንጂ የመጨረሻ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ እና የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥን "ለመቆጣጠር" እና ነዋሪዎቿን በግዳጅ ለማዛወር የያዙትን እቅድ አውግዘዋል። መሪዎቹ ይህንን ሀሳብ ሕገ-ወጥ የዘር ማጽዳት ሲሉ ገልፀውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X