"የብሪክስ ትብብር ለዘላቂ ልማት እና ለአዲስ የዓለም ሥርዓት ቁልፍ ነው"
19:39 16.05.2025 (የተሻሻለ: 19:54 16.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የብሪክስ ትብብር ለዘላቂ ልማት እና ለአዲስ የዓለም ሥርዓት ቁልፍ ነው"
የብሪክስ መድረክ በዋነኝነት እያደጉ ያሉ ሀገራትን ያቀፈና ቴክኖሎጂ በመካከላቸው ያሉትን ልዩነቶች እያጠበበ ነው ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የብሪክስ የክህሎት ባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ማፑሌ ንካንይዋ በሞስኮ በተካሄደው የብሪክስ የሴት ሥራ ፈጣሪዎች ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በጋራ መርሆዎች እና በሴቶች በዳበሩ ቴክኖሎጂዎች ላይ የተመሠረተ የኩባንያዎች ትብብር የገበያ ስኬትን ያረጋግጣል ያሉት ንካንይዋ ለብሪክስ ዓለም አቀፋዊ መሪነት ክልላዊ ግንዛቤ ቁልፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
ንካንይዋ በተለይም በፋይናንስ፣ በማዕድን እንዲሁም በመረጃ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የአፍሪካን የአረንጓዴ የገበያ አቅም አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X