የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር አሁናዊ መረጃዎች ፦
17:47 16.05.2025 (የተሻሻለ: 18:04 16.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር አሁናዊ መረጃዎች ፦
▪ ዛሬ ጠዋት የዩክሬን ልዑካን ከአሜሪካ እና ቱርክ ተወካዮች ጋር በኢስታንቡል ተወያይተዋል።
▪የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ቀጥሎ የተደረገው ውይይት ለጋዜጠኞች ዝግ ነበር።
▪ ድርድሩ ለሁለት ሰዓታት ያህል ቆይቷል።
▪ከድርድሩ መጠናቀቅ በኋላ የሩሲያ ዋና ተደራዳሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ መግለጫ ሰጥተዋል።
▪የሩሲያ ልዑካን በድርድሩ ውጤት አጥጋቢ እንደነበር ፣ 1 ሺህ የጦር እስረኞችን ለመለዋወጥ እንደ ተስማሙ እንዲሁም ሞስኮ ንግግሩን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ዋና ተደራዳሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።
▪ከድርድሩ በኋላ ዜለንስኪ፣ ማክሮን፣ ሜርዝ፣ ስታርመር እና ቱስክ ከትራምፕ ጋር ተነጋግረዋል።
▪ ትራምፕ ዛሬ ምሽት የዩክሬንን የሰላም ጉዳይ ለመወያየት ለፑቲን ሊደውሉ እንደሚችሉ አሳዉቀዋል።
▪የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደገለጹት በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች ሰላምን ለማምጣት እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
▪የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን ሌላ ዙር ስብሰባ ለማድረግ መሰረታዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X