በኢስታንቡል በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር አሁናዊ መረጃዎች፦
14:45 16.05.2025 (የተሻሻለ: 17:34 16.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢስታንቡል በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ድርድር አሁናዊ መረጃዎች፦
🟠 ድርድሩ በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ተጀምሯል።
🟠 የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን "ሰላም መፍጠር" ወይም "አውዳሚው ግጭት ይቀጥል" የሚለውን በራሳቸው መወሰን አለባቸው ሲሉ ፊዳን ተናግረዋል።
🟠 በድርድሩ ላይ ፑቲን እና ዘለንስኪ ሊገናኙ ስለሚችሉበት መንገድ ውይይት ይደረጋል።
🟠 በኢስታንቡል ከሩሲያ ጋር ድርድር ከመጀመሩ በፊት የዩክሬን ልዑክ መሪ ሩስተም ኡሜሮቭ የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታ አቅርበዋል።
🟠 በዕለቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ፣ የዩክሬን እና የቱርክ ልዑካን ስብሰባ ተካሂዷል።
🟠 የዩናይትድ ስቴትስ፣ የዩክሬን እና የቱርክ ሶስትዩሽ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን የሀገር ደህንነት አማካሪዎች ጋር ተነጋግረዋል።
🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስለሚያደረጉት ስብሰባ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X