በኢስታንቡል የሚገኘው የሩሲያ ልዑካን ዝግጁ ሆኖ በመጠበቅ ላይ ይገኛል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገለጹ
15:12 15.05.2025 (የተሻሻለ: 15:34 15.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢስታንቡል የሚገኘው የሩሲያ ልዑካን ዝግጁ ሆኖ በመጠበቅ ላይ ይገኛል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢስታንቡል የሚገኘው የሩሲያ ልዑካን ዝግጁ ሆኖ በመጠበቅ ላይ ይገኛል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገለጹ
ዲሚትሪ ፔስኮቭ በኢስታንቡል የሚደረገውን ድርድር አስመልክቶ የሰጧቸው ዋና ዋና መግለጫዎች፦
▪ ፑቲን ትናንት ምሽት አግባብነት ባላቸው ሪፖርቶች ላይ ከተወያዩ በኋላ የድርድሩን አቋም ለሩሲያ ልዑካን ቡድን አሳውቀዋል።
▪ የሩሲያ ልዑካን ከጠዋቱ ጀምሮ ኢስታንቡል ውስጥ ይገኛሉ።
▪ ሞስኮ እስካሁን የዩክሬን ልዑካን ስብጥርን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ የላትም።
▪ ሩሲያ በኢስታንቡል ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗ አስቀድሞ የታወቀ ነው።
▪ ሩሲያ በኢስታንቡል የሚደረገው ድርድር ውጤታማ እንዲሆን ጥረት ለማድረግ ዝግጁ ነች።
▪ በኢስታንቡል የሚገኙ የሩሲያ ተደራዳሪዎች "እንደ አስፈላጊነቱ" ለፑቲን ሪፖርት ያደርጋሉ።
▪ፑቲን በቅርብ ቀናት ውስጥ ኢስታንቡልን የመጎብኘት እቅድ የላቸውም።
▪ በቅርብ ቀናት ውስጥ በፑቲን እና በትራምፕ መካከል ለሚደረግ ስብሰባ ዝግጅት እየተደረገ አይደለም፤ ጉዳዩ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ውይይት አልተደረገበትም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X