ሞስኮ ዘለንስኪ በሩሲያ የልዑካን ቡድን ዙሪያ የሰጠውን አስተያየት አወገዘች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሞስኮ ዘለንስኪ በሩሲያ የልዑካን ቡድን ዙሪያ የሰጠውን አስተያየት አወገዘች
ሞስኮ ዘለንስኪ በሩሲያ የልዑካን ቡድን ዙሪያ የሰጠውን አስተያየት አወገዘች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.05.2025
ሰብስክራይብ

ሞስኮ ዘለንስኪ በሩሲያ የልዑካን ቡድን ዙሪያ የሰጠውን አስተያየት አወገዘች

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ትችት ዘለንስኪ ወደ ኢስታንቡል የተላከውን የሩሲያ ልዑክ “የይስሙላ” ማለቱን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

ዛካሮቫ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 በኢስታንቡል የሚደረገው ድርድር ቱርክ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት ወደ አመሻሽ ተዛውሯል።

🟠 በኢስታንቡል በሚደረገው ንግግር ዙሪያ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቢሮ የሚወጡ ተቃራኒ መግለጫዎች ኪዬቭ ትዕይንት ለመፍጠር እየሞከረች እንደሆነ አስመስሎታል።

🟠 ሩሲያ በኢስታንቡሉ ድርድር እውነተኛ እና የችግሩን መንስዔዎች ለመፍታት ዝግጁ ናት።

🟠 በርሊን፣ ፓሪስ እና ለንደን የጦር መሳሪያ አቅርቦትን ጨምሮ ኪዬቭን መደግፍ የሚቀጥሉ ከሆነ በድርድሩ ጠረጴዛ ቦታ ሊኖራቸው አይችልም፡፡

🟠 ሞስኮ የትራምፕ አስተዳደር ፔንታጎን ለዩክሬን ጦር የባዮሎጂ ፕሮግራም የሚያደርገውን ድጋፍ ለመፍታት እርምጃዎችን እንደሚወስድ ተስፋ ታደርጋለች፡፡

🟠 ኪዬቭ ድርድሩን ባስተጓጎለች ቁጥር ዩክሬን እያነሰች ትመጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0