ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን "ፈሪዎች" ሲሉ ወቀሱ
17:36 14.05.2025 (የተሻሻለ: 17:54 14.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን "ፈሪዎች" ሲሉ ወቀሱ
የትራምፕ አስተዳደር መድልዎ ደርሶባቸዋል ብሎ የጥገኝነት መብት የሰጣቸው 'አፍሪካነሮች' ሰኞ እለት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎስ ይህን ክስ ውድቅ አድርገው፤ የሸሹት በአፓርታይድ ዘመን ያልነበረውን እኩልነት ለማምጣት የሚደረገው ጥረት ስላልተመቻቸው ነው ብለዋል።
"እኛ ደቡብ አፍሪካውያን ጠንካሮች ነን። ከችግሮቻችን አንሸሽም። እዚህ ሆነን ችግሮቻችንን እንፈታለን። መሸሽ የፈሪ ነው፤ የወሰዳቹት እርምጃ የፈሪ ነው" ብለዋል።
ራማፎሳ ዶናልድ ትራምፕ እና ኤለን መስክ በነጭ ገበሬዎች ላይ "ዘር ማጥፋት" ተፈፅሟል በማለት ላቀረቡት ክስ በአቢጃን በተካሄደው የአፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።
"በአህጉሪቱ ውስጥ ቅኝ ገዥዎች መጥተው የቆዩባት ብቸኛ ሀገር የኛ ናት፤ ከሀገራችን በጭራሽ አላባረርናቸውም።"
ፕሬዝዳንቱ የሄዱት ሰዎች የስደተኝነት መስፈርቶችን እንደማያሟሉ አጽንኦት በመስጠት፤ በቅርቡ ከትራምፕ ጋር በሚኖራቸው ግኑኝነት ጉዳዩን በቀጥታ እንደሚያነሱ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X