የእንግሊዝ የጦር ወንጀሎች ዓለም አቀፍ እምነትን አናግተዋል፤ 'ዓለም አቀፉን ሥርዓት ተጥሏል’ ሜክሲኮዊዉ የታሪክ ምሁር
16:42 14.05.2025 (የተሻሻለ: 17:04 14.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእንግሊዝ የጦር ወንጀሎች ዓለም አቀፍ እምነትን አናግተዋል፤ 'ዓለም አቀፉን ሥርዓት ተጥሏል’ ሜክሲኮዊዉ የታሪክ ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የእንግሊዝ የጦር ወንጀሎች ዓለም አቀፍ እምነትን አናግተዋል፤ 'ዓለም አቀፉን ሥርዓት ተጥሏል’ ሜክሲኮዊዉ የታሪክ ምሁር
በአፍጋኒስታን የእንግሊዝ ወታደሮች ሲቪሎች ላይ የፈፀሙት ግድያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በተመሠረተው የሕግ ሥርዓት ውስጥ ጥልቅ ክፍተት እንዳለ ያሳያል ሲሉ ጃቪየር ጋሜዝ ቻቬዝ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
ከትንታኔያቸው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-
⏺ ተፈፅመዋል የተባሉት የጦር ወንጀሎች ኃያላን መንግሥታት የስትራቴጂክ የበላይነታቸውን የሚያሳዩበት አንድ መንገድ ነው።
“በመካከለኛው ምሥራቅ የተካሄዱትን ጨምሮ አብዛኞቹ የዘመኑ ጦርነቶች የዚህ ዑደት አንድ አካል” እና ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ የኃይል ለውጦች እና የካፒታሊስት ጣልቃ ገብነት ጋር የተያያዙ ናቸው።
⏺ የምዕራባውያን ሚዲያዎች እና መንግሥታት “አውሮፓን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አድርገው ይስላሉ”፤ እውነታው ግን የቅኝ ግዛት ዓይነት ጦርነቶች ደጋፊዎች መሆናቸው ነው።
ቻቬዝ አክለውም የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሚዛናዊነት ይጎድለዋል ብለዋል፦
▫የምዕራባውያን ሀገራት ወታደሮችን መክሰስ “እጅግ በጣም ከባድ” ነው።
▫“አብዛኛውን ግዜ በፍርድ ቤቱ የሚቀርቡት የደቡባዊው ዓለም ዜጎች እንጂ ከዋና ዋና ምዕራባውያን ሀገራት አይደለም።”
የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች መጠቀሚያ እየሆኑ እንደሆነና ሞራላዊ ስያሜ በመስጠት ደም አፋሳሽ ጣልቃ ገብነታቸውን በመደበቅ ምዕራባውያኑ ከመጠየቅ እያመለጡ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X