የአፈር መዳበሪያ የጫነች 22ኛዋ የኢትዮጵያ መርከብ የፊታችን እሁድ ጅቡቲ ትደርሳለች
16:39 14.05.2025 (የተሻሻለ: 17:34 14.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፈር መዳበሪያ የጫነች 22ኛዋ የኢትዮጵያ መርከብ የፊታችን እሁድ ጅቡቲ ትደርሳለች
መርከቧ 55 ሺህ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ መጫኗን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ አስታውቋል።
ለ2017/18 ምርት ዘመን የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎች፦
እስካሁን በ21 መርከቦች 1 ሚሊየን 141ሺ 418.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ደርሷል።
ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ
1 ሚሊዮን 103ሺ 113.3 ሜትሪክ ቶን ወደ ሀገር ገብቷል፣
ጅቡቲ ወደብ ላይ 38ሺ 304.9 ሜትሪክ ቶን አፈር ማዳበሪያ ይገኛል፣
ወደብ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ተሽከርካሪዎችን እና ባቡር በመጠቀም ከ150 በላይ ወደሆኑ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ተጓጉዟል፡፡
22ኛዋ መርከብ በመጪው እሁድ 55 ሺህ 660 ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ ዓይነት ጭና ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች።
በሰው ሰራሽ የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X