ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ሰበሰበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ሰበሰበች
ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ሰበሰበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.05.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከቡና የወጪ ንግድ በሀገሪቱ ታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ሰበሰበች

ባለፉት 10 ወራት ወደ ውጪ ከተላከ ቡና ከ1 ነጥብ 8 ቢልየን ዶላር በላይ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ አፈጻጸም በቁጥሮች፦

ሀገሪቱ በበጀት ዓመቱ አሥር ወራት ከ354 ሺህ ቶን በላይ ቡና ልካ 1 ነጥብ 868 ቢሊየን ዶላር ገቢ መሰብሰብ ችላለች።

አፈፃፀሙ በምርት ረገድ የ70 በመቶ ጭማሪ እንዲሁም በገቢ ረገድ የ87 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የኢትዮጵያ ቡና ምርት ቀዳሚ መዳረሻ ሀገራት፦

ጀርመን ከ61 ሺህ ቶን በላይ ቡና ተልኮ ከ295 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

ሳዑዲ አረቢያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ተልኮ ከ290 ሚልየን ዶላር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከ28 ሺህ ቶን በላይ ቡና የተላከ ሲሆን 192 ሚልየን ዶላር ማግኘት ተችሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0