ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ያጋጠመው የፋይናንስ እጥረት እንዳሳሰባት ገለፀች
12:45 14.05.2025 (የተሻሻለ: 13:04 14.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ያጋጠመው የፋይናንስ እጥረት እንዳሳሰባት ገለፀች
በአፍሪካ ሕብረት እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በተወያዩበት ወቅት የተናገሩት ነው፡፡
ሶማሊያ በዘላቂነት እንድትረጋጋ የሚሠራው ተልዕኮ ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለዋል።
በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም አዝጋሚ እንደሆነና ይህም በሀገሪቱ መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተናግረዋል።
የሕብረቱ ሊቀመንበር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለቀጣናው መረጋጋት የምታደርገው ድጋፍ የሚወደስ እና ሊቀጥል የሚገባው ነው ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X