የጭካኔ ቁንጮዎች፦ ምስክሮች የእንግሊዝ ልዩ ኃይሎች በኢራቅና አፍጋኒስታን የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ወንጀሎች አጋለጡ

ሰብስክራይብ

የጭካኔ ቁንጮዎች፦ ምስክሮች የእንግሊዝ ልዩ ኃይሎች በኢራቅና አፍጋኒስታን የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ወንጀሎች አጋለጡ

🪖 ቢቢሲ አዳዲስ የዓይን እማኞችን አመሳክሮ የሠራው ዘገባ የእንግሊዝ ልዩ ክፍለ ጦሮች ከአሥር ዓመታት በላይ በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ጭካኔ የተሞላባቸውን ድርጊቶች መፈፀማቸውን አጋልጧል።

ክሱ የእንግሊዝ ጦር ልዩ አየር ኃይል እና የሮያል ባህር ኃይል ልዩ የጀልባ አገልግሎትን ተጠያቂ አድርጓል።

የፈፀሙት ወንጀል የሚከተሉትን ያካትታል፦

▪ያልታጠቁ ወንዶችን ህፃናትን ጨምሮ እጃቸው በታሠረበት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መግደል።

▪በሌሊት ወረራ ወቅት ንፁሃን ዜጎችን በተኙበት መግደል።

▪የፈጸሙትን ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ለመሸፈን በሬሳ ላይ የጦር መሣሪያ ማስቀመጥ እና ራስን ለመከላከል እንደተደረገ ለማስመሰል መሳሪያዎችን ማስወገድ።

▪የታሰሩ ሰዎችን "በመደበኛ የአሠራር ሂደት" የበታች ወታደሮች በበላይ አለቆቻቸው በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት ግድያ መፈፀም።

▪የቆሰሉትን ገድሎ ማለፍ ይገኙበታል።

  አንድ የዓይን እማኝ እንደተናገሩት "አንድን ሰው ይፈትሹታል፣ ቀጥሎም በሰንሰለት ያስሩታል፣ ከዚያም ይገድሉታል ከዚያም ሰውዬውን ለማሰር የተጠቀሙበትን የፕላስቲክ ሰንሰለት ቆርጠው በሬሳው አጠገብ ሽጉጥ ያስቀምጣሉ" ብለዋል።

ችላ የተባሉ ማስጠንቀቂያዎች፡-

በወቅቱ የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሃሚድ ካርዛይ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ዴቪድ ካሜሮን በብሪታንያ ልዩ ኃይሎች ስለተፈጸሙት የሲቪል ሰዎች ግድያ በግል አስጠንቅቀዋቸው ነበር ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0