"የአፍሪካ የተደበቁ የጂኦሎጂ ሀብቶች ዓለም አቀፋዊ እይታ ይገባቸዋል"
16:36 13.05.2025 (የተሻሻለ: 16:54 13.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የአፍሪካ የተደበቁ የጂኦሎጂ ሀብቶች ዓለም አቀፋዊ እይታ ይገባቸዋል"
አፍሪካ ከፍተኛ የሥነ-ምድር ሀብት ቢኖራትም ዓለም ይህንን እምብዛም አያውቅም ሲሉ የዩኔስኮ ተወካይ ተናግረዋል።
በአህጉሪቱ ሁለት ብቻ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ (በሞሮኮ እና በታንዛኒያ) ጂኦ ፓርኮች እንደሚገኙ በመግለፅ አስፈላጊ እርምጃ መወሰድ አለበት ሲሉ በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን እና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የዩኔስኮ ግንኙነት ቢሮ ዳይሬክተር ሪታ ቢሱናዝ አሳስበዋል፡፡
"አፍሪካ ብዙ አቅም አላት...እኛ ማድረግ ያለብን ነገር ስለ ጂኦሎጂካዊ ቅርሳችን የበለጠ ግንዛቤ መያዝ፣ የተሻለ ቅንጅት መፍጠር እና በተጨማሪም አቅማችንን መገንባት ነው" በማለት ዳይሬክተሯ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በተካሄደው ቀጣናዊ አውደ ጥናት ላይ ንግግር ያደረጉት ቢሱናዝ ዝግጅቶች ከወዲሁ መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
"የ45 የአፍሪካ ሀገራትን አቅም ገንብተናል...አሁን የሚያስፈልገን የዕጩዎች ዝርዝር ማዘጋጀት፣ ማቅረብ እና ከዚያ ሌላው ይከተላል" ብለዋል።
የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦ ፓርኮች ዘላቂ የቱሪዝም፣ የትምህርት እና የማሕበረሰብ ልማትን የሚያበረታቱ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምድር ጠቀሜታ ያላቸውን አካባቢዎች የሚያሳዩ ነጠላ፣ የተዋሃዱ ማዕከላት ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X