ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ይበልጥ ራሷን እየቻለች እንደሆነ ሪፖርት አመለከተ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ይበልጥ ራሷን እየቻለች እንደሆነ ሪፖርት አመለከተ
ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ይበልጥ ራሷን እየቻለች እንደሆነ ሪፖርት አመለከተ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.05.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ይበልጥ ራሷን እየቻለች እንደሆነ ሪፖርት አመለከተ

የአሜሪካ የግብርና ሚኒስቴር ባወጣው ዓመታዊ የዓለም የእህል ምርት ሪፖርት መሠረት እ.ኤ.አ በ2025-26 ኢትዮጵያ ከውጭ የምትገዛው የስንዴ እና የስንዴ ምርት መጠን በ24 በመቶ ይቀንሳል።

“በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም፤ የሀገር ውስጥ አቅርቦት በሂደት እየተሻሻለ በመምጣቱ የገቢ መጠን ይቀንሳል” ሲል ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የሀገር ውስጥ የስንዴ ምርት ከዓመት እስከ ዓመት 5 በመቶ በመጨመር ክብረ ወሰን የሆነ 6 ነጥብ 5 ቶን የስንዴ ምርት በዚሁ የምርት ዘመን እንደሚጠበቅ ሪፖርቱን ጠቅሶ ወርልድ ግሬን ድረ-ገጽ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ የእህል ፖሊሲ የምግብ ዋስትና እና ከሀገር ውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ላይ ያተኮረ ነው ያለው ሪፖርቱ፤ መንግሥት እየመራው ባለው ጥረት ምክንያት በሀገር ውስጥ የእህል ምርት ከፈተኛ መሻሻል ታይቷል ብሏል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0