የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ ከ40 ቢሊየን ዶላር ማለፉ ተገለፀ
13:38 13.05.2025 (የተሻሻለ: 13:54 13.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ ከ40 ቢሊየን ዶላር ማለፉ ተገለፀ
የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ፎረም ላይ እንደተናገሩት 80 በመቶ የሚሆኑት የቅርብ ገዜ ኢንቨስትመንቶች ከሀገር ውስጥ ሀብቶች የመጡ ናቸው።
ሚኒስትር ዲኤታው ኢትዮጵያ ለማክሮ ኢኮኖሚው መረጋጋት እና ለተሟላ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጥ ቁርጠኛ እንደሆነችም አስረግጠዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ መከተል የጀመረችው የገንዘብ ፖሊሲ የወጪ ንግድ በእጥፍ እንዲጨምር፣ የማዕከላዊ ባንክ የገንዘብ ክምችት በሶስት እጥፍ እንዲያድግ እና ከውጭ የሚላከው ገንዘብ የ25 በመቶ ጭማሬ እንዲያሳይ ማድረጉን የተናገሩት ደግሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X