የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከህንድ ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከህንድ ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ተነገረ
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከህንድ ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.05.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከህንድ ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉ ተነገረ

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዳኤታ ጂቴንድራ ሲንግ በተለይም ሀገራቸው በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት እና በአይሲቲ ዘርፎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል።

ባለሥልጣኑ ይህን ያሉት በህንድ ጉብኝት ላይ ከሚገኘው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑካን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

አክለውም ከ650 በላይ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እያደረጉ እንደሆነና በአጠቃላይ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የውጭ ቀጣሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0