'ሩሲያ ለዓለም ሰላም ለማምጣት የተከተለችውን የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ' ኢትዮጵያዊዉ ፖለቲከኛ አወደሱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'ሩሲያ ለዓለም ሰላም ለማምጣት የተከተለችውን የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ' ኢትዮጵያዊዉ ፖለቲከኛ አወደሱ
'ሩሲያ ለዓለም ሰላም ለማምጣት የተከተለችውን የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ' ኢትዮጵያዊዉ ፖለቲከኛ አወደሱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.05.2025
ሰብስክራይብ

'ሩሲያ ለዓለም ሰላም ለማምጣት የተከተለችውን የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ' ኢትዮጵያዊዉ ፖለቲከኛ አወደሱ

"ሰላምን ለማዘግየት ምክንያት የለም” በዚህም የፑቲን የሰላም ውይይት ሃሳብ በጣም “ወሳኝ፣ አስፈላጊ እና ወቅታዊ ነው" ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲህ መኸዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

"የቅድመ ሁኔታ አለመኖር ሁለቱ ወገኖች በተለይም በሩሲያ በኩል ግልፅ እና መፍትሄ የሚያመጣ ውይይት ለማድረግ ፈቃደኝነቱ እንዳለ ያሳያል" ብለዋል ፖለቲከኛው።

እንደ ፈቲህ ገለፃ ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚደርግ ቀጥተኛ ውይይት፦

⦁ በስጋቶች ዙሪያ መግባባት እንዲኖር በማድረግ፤ ስሁት ትርጓሜዎችን ይቀንሳል፡፡

⦁ ተቀባይነት ያላቸው እና ውጤታማ የመፍትሄ አማራጮችን ያበረታታል፡፡

⦁ ውይይቱ በግጭቱ ዋና ዋና መንስዔዎች ላይ ያተኮረ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

⦁ ለማመቻመች በር ይከፍታል።

የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ሰላም-ተኮር ስትራቴጂ፦

⦁ ዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረትን ይቀንሳል፣

⦁ ግጭቱ ተባብሶ እንዳይቀጥል እና ዓለም አቀፍ ቅርጽ እንዳዪዝ ያግዛል፣

⦁ ዓለም አቀፍ ንግድ እና የኃይል ግብይትን ያረጋጋል፣

⦁ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ያሻሽላል፣ የዋጋ ግሽበትን ይቀንሳል፣ በተለይም ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እፎይታን ያመጣል ብለዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0