"የጥቁር ዘር ጥቁሮችን ለማጥቃት መጠቀሚያ መሆን የለበትም" ሲሉ ኢብራሂም ትራኦሬ አፍሪኮምን ተቹ

ሰብስክራይብ

"የጥቁር ዘር ጥቁሮችን ለማጥቃት መጠቀሚያ መሆን የለበትም" ሲሉ ኢብራሂም ትራኦሬ አፍሪኮምን ተቹ

ትራኦሬ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ በቡርኪና ፋሶ የውጭ ሀገራት ግኑኝነት እና የማዕድን ሀብት ገቢ አያያዝ ዙሪያ ያቀረቡትን መሠረተ ቢስ ክስ አጥብቀው አስተባብለዋል።

"ከፈለግነው ጋር ግንኙነት መመሥረት እንችላለን - ነፃነት ማለት ይሄ ነው" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ስለ ቡርኪና ፋሶ ወርቅ የተሰነዘሩ "ውሸቶችን" አጋልጠዋል፡፡

"በቡርኪና ግምጃ ቤት ወርቅ ማከማቸት የጀመርነው እኛ ነን። ይህ ባይሆን ኖሮ በቡርኪና አንድ ግራም የወርቅ ክምችት አይኖርም ነበር።"

ትራኦሬ ይፋዊ ይቅርታም ጠይቀዋል "ራሱን በመመልከት፣ ሀፍረት ሊሰማው እና በይፋ መጥቶ፤ የተሳሳተ መረጃ ደርሶኛል፡፡ በግልጽ ይቅርታ እጠይቃለሁ ሊል ይገባል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0