"ሉዓላዊነት የሚጀምረው ከሠራዊት ነው" ኢብራሂም ትራኦሬ
16:47 12.05.2025 (የተሻሻለ: 17:04 12.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ሉዓላዊነት የሚጀምረው ከሠራዊት ነው" ኢብራሂም ትራኦሬ
የቡርኪና ፋሶው ፕሬዝዳንት የምዕራባውያን ወታደሮች ሽብርተኝነትን "አባብሰዋል" ሲሉ ከሰዋል። የውጭ ኃይሎች ምልመላን እና የመሣሪያ አቅርቦትን በማገድ የቡርኪና ፋሶን ብሔራዊ ሠራዊት አዳክመዋል ብለዋል።
"በሳንካራ ዘመን እንኳን ከ10 እና 20 ዓመታት በኋላ ከነበረን የተሻለ መሣሪያ ነበረን" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ለሽብርተኝነት ዝግጁ እንዳልነበረችም ነው በንግግራቸው የጠቆሙት።
"ስቃይ እየደረሰብን ነው፤ ግን ሠራዊት መገንባት አለብን። ከዚህ ጦርነት ስንወጣ የበለጠ ጠንካራ ሆነን መውጣት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።"
ሉዓላዊ ወታደራዊ ኃይል ኢኮኖሚውን፣ ትምህርትን እና ልማትን ነጻ ለማውጣት ቁልፍ ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሶቪየት ሕብረት እንዳደረገቸው ቡርኪና ፋሶም ፈተናዎቿን ወደ ጥንካሬ ለመቀየር ታስባለች ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X