የመጀመሪያዎቹን 49 ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን የጫነው አውሮፕላን ወደ አሜሪካ በረረ
16:28 12.05.2025 (የተሻሻለ: 16:44 12.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የመጀመሪያዎቹን 49 ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን የጫነው አውሮፕላን ወደ አሜሪካ በረረ
ትራምፕ አወዛጋቢ የስደተኞች ፕሮግራማቸውን ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን "ለ ኢ-ፍትሃዊ የዘር መድልዎ ኢላማዎች ናቸው" በማለት መከላከላቸው ይታወሳል። የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የትራምፕን ፖሊሲ ፖለቲካዊ እና የሀገሪቱን ሕገ-መንግስታዊ ዴሞክራሲ የሚጎዳ ሲሉ በጥብቅ ተቃውመውታል።
ፕሪቶሪያ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን አሁንም በሀገሪቱ ውስጥ እጅግ ሀብታም ከሆኑ የሕብረተስብ ክፍሎች መሆናቸውን፣ 75% የሚሆነውን የግል መሬት እንደሚቆጣጠሩና ከአብላጫው የጥቁር ሕዝብ በ20 እጥፍ የበለጠ ሀብት እንዳለቸው አስረድታለች።
የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የትራምፕ እርምጃ እውነታውን የሚያዛባ ከመሆኑም በላይ አስተዳደራቸው ነጭ ያልሆኑ ስደተኞች ላይ ከያዘው ጥገኝነትን የመገደብ ፖሊሲ ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X