አፍሪካ ውስጥ ሁለት ጂኦ ፓርኮች ብቻ መመዝገባቸው "አሳዛኝ" ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሚኒስትር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ ውስጥ ሁለት ጂኦ ፓርኮች ብቻ መመዝገባቸው "አሳዛኝ" ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሚኒስትር ተናገሩ
አፍሪካ ውስጥ ሁለት ጂኦ ፓርኮች ብቻ መመዝገባቸው አሳዛኝ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሚኒስትር ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.05.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ውስጥ ሁለት ጂኦ ፓርኮች ብቻ መመዝገባቸው "አሳዛኝ" ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሚኒስትር ተናገሩ

ይህንን እውነታ ለመቀየር ያሰበ ቀጣናዊ መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ጋር በመተባበር ያሰናዳው ዝግጅት በዘርፉ ኢትዮጵያ የያዘችውን አቅም አጉለቶ ለማሳየት ያለመ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጂኦ ፓርኮችን ማስመዝገቧ ለምርምር እንደሚጠቅም፣ በዙሪያቸው ያሉ ማሕበረሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና ዓለም አቀፍ እውቅናን እንዲያገኙ እድል እንደሚፈጥር የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ጂኦ ፓርኮች ቁጥር 229 እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጂኦ ፓርክነት ልታስመዘግባቸው የሚችሉ ብዙ ቦታዎች እንዳሏት የጠቆሙም ሲሆን ለማሳያነት በጠቀሱት መልካ ቁንጥሬ የመድረኩ ተሳታፊዎች ምልከታ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

መልካ ቁንጥሬ መካነ ቅርስን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ለዩኔስኮ ሠነድ መላኩ የሚታወስ ነው፡፡ ቦታው የሰው ልጅ፣ የእንስሳትና የጥንት የሰው ልጅ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ይነገራል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0