አዲስ አበባ የ4ኛው የክህሎት ኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ ሆነች

© telegram sputnik_ethiopiaአዲስ አበባ የ4ኛው የክህሎት ኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ የ4ኛው የክህሎት ኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ ሆነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.05.2025
ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ የ4ኛው የክህሎት ኢትዮጵያ ውድድር አሸናፊ ሆነች

መድረኩ ኢትዮጵያ ብቃትና ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች እንዳሏት ያረጋገጠ ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል።

የውድድሩ አሸናፊዎች፦

አዲስ አበባ 10 የወርቅ፣ 4 የብር እና 4 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።

የኦሮሚያ ክልል በ5 ወርቅ፤ በ10 ብር እና በ6 ነሀስ ሁለተኛ ወጥቷል።

አማራ ክልል በ2 ወርቅ፣ በ5 ብር እና በ6 የነሀስ ሜዳሊያዎች የሦስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።

በክህሎት፣ በቴክኖሎጂና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ልህቀት ያሳዩ ዜጎች የተፎካከሩበት ውድድር ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0