የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ከኒጄር አቻቸው ጋር ተወያዩ
20:30 10.05.2025 (የተሻሻለ: 20:54 10.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ከኒጄር አቻቸው ጋር ተወያዩ
በሁለትዮሽ ስብሰባው ላይ አንድሬ ቤሎሶቭ ያስተላለፏቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 ቤሎሶቭ ሞዲ በድል ቀን ክብረ በዓል ላይ በመገኘታቸው ምስጋናቸውን ገልጸዋል፣
🟠 ሚኒስትሩ ለበዓሉ መምጣታቸው ፋሺዝም ላይ የተገኘው ድል የጋራ መሆኑን ያረጋግጣል፣
🟠 ሩሲያ ወታደራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንዲሁም የሳህል ጥምረት ሀገራት አዲስ ቀጣናዊ የደህንነት መዋቅር እና ገለልተኛ የውጭ ፖሊሲ ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ትደግፋለች፤
🟠 ከአፍሪካ አጋሮች ጋር የሚደረገው ትብብር የሩሲያ ፕሬዝዳንት በበላይነት የያዙት ቀዳሚ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው፣
የኒጄር መከላከያ ሚኒስትር ሳሊፉ ሞዲ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 ሞዲ ለድል ቀን በዓል ግብዣ ቤሎሶቭን አመስግነዋል፣
🟠 ሚኒስትሩ ሩሲያ ለኒጄር እና ለሳህል ኮንፌዴሬሽን ለምትሰጠው ትኩረት እና ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
በስብሰባው ሁለቱ ወገኖች የሩሲያ እና ኒጄር የመከላከያ ተቋማት በአሁኑ ሰዓት እየተባበሩባቸው ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
