ኢብራሂም ትራኦሬ በሞስኮ በሳህል ሀገራት ጥምረት የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ስብሰባ መሩ
19:44 10.05.2025 (የተሻሻለ: 20:04 10.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢብራሂም ትራኦሬ በሞስኮ በሳህል ሀገራት ጥምረት የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ስብሰባ መሩ
የበርኪናፋሶው መሪ ከጥምረቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን የበርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ገልጿል። ስብሰባው ግንቦት 1 ከሰዓት ተካሂዷል ተብሏል።
የመከላከያ ሚኒስትሮቹ በጥምረት ሀገራቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ሪፖርት አቅርበዋል። ትራኦሬ "ሽብርተኝነትን ለመግታት በሚደረገው ትግል የበለጠ አዎንታዊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ አዳዲስ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።"
የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ "በተለይም መሬት ላይ ድሎችን እያስመዘገበ ስላለው የጥምረቱ የተባበረ ኃይል ትግበራ ዙሪያ የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶችን ገምግመናል" ብለዋል።
ኢብራሂም ትራኦሬ ናዚ ጀርመን ድል የተደረገበት 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ሞስኮ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ