በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ልዑክ ቆይታ በታቃውሞ ታጅቦ ለአንድ ዓመት ተራዘመ
19:07 10.05.2025 (የተሻሻለ: 19:24 10.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ልዑክ ቆይታ በታቃውሞ ታጅቦ ለአንድ ዓመት ተራዘመ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ልዑክ ቆይታ በታቃውሞ ታጅቦ ለአንድ ዓመት ተራዘመ
▪አስራ ሁለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ድጋፍ በሰጡበትና ሩሲያ፣ ቻይና እና ፓኪስታን ድምጸ ተዓቅቦ ባደረጉበት ውሳኔ ሰላም አስከባሪ ኃይሉ እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲቆይ ፀድቋል።
▪በአሜሪካ የቀረበው ረቂቅ ውሳኔ በጾታ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ለተወሰነ ግዜ ተራዝሞ ነበር።
ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ የሩሲያ፣ የቻይና እና የፓኪስታን ተወካዮች ትችቶችን አሰምተዋል። ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮን ሥራ ብትደግፍም፤ አሜሪካ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ላይ "ጫና እያሳደረች ነው" ስትል ከሳለች።
በተመሳሳይ ቻይና ውሳኔው "በመሬት ላይ ያለውን እውነታ" ያላንፀባረቀ "ከመጠን በላይ ጫና" ፈጥሯል ስትል ተከራክራለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X