ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ መቀላቀሏ የፋይናንስ ድጋፍ ምንጯን ያሰፋል ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
17:59 10.05.2025 (የተሻሻለ: 18:14 10.05.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ መቀላቀሏ የፋይናንስ ድጋፍ ምንጯን ያሰፋል ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ መቀላቀሏ የፋይናንስ ድጋፍ ምንጯን ያሰፋል ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
ኢትዮጵያ አዲሱን የልማት ባንክ እንድትቀላቀል ከአባል ሀገራቱ ፍቃድ ማግኘቷን ተከትሎ ለሀገሪቱ ምን አይነት ጥቅም እንዳለው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቃለ ምልልሰ ያደረጉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሽመልስ አርዓያ አብራርተዋል።
"ለኢትዮጵያ የገንዘብ ምንጮችን ለማስፋት እና በተመሳሳይ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ ተፅዕኖዋን ለማሳደግ ጥሩ አጋጣሚ ነው" ብለዋል።
ከተለያዩ አበዳሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚገኘው የገንዘብ ድጋፍ እያደገ ላለው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ወሳኝ መሆኑንሞ አስረድተዋል።
"ኢትዮጵያ የፈንድ ምንጮችን እያሰፋች ያለችው ኢኮኖሚያዋ እያደገ በመምጣቱ ነው። የተሻለ የብድር አማራጭ እንዲሁም እንደ የአዲሱ የልማት ባንክ ካሉ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ብድር ማግኘት ጥሩ አማራጭ ነው፤ ምክንያቱም የሁለትዮሽ አበዳሪዎች ወይም የኮሜርሻል አበዳሪዎች የወለድ መጠን ከፍተኛ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው በምዕራቡ ዓለም የተቋቋሙት የገንዘብ ተቋማት የብድር አሰጣጥ ሂደት አሉታዊ ሊባሉ በሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች የተሞሉ እንደሆነም አስረድተዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X