ዩናይትድ ስቴትስ ለአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንዳቆመች ዘገባዎች አመላከቱ
15:26 10.05.2025 (የተሻሻለ: 15:44 10.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩናይትድ ስቴትስ ለአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንዳቆመች ዘገባዎች አመላከቱ
ዋሽንግተን ለአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጊያ ተልዕኮ (አውሶም) አሁን ባለበት ሁኔታ የገንዘብ ድጋፍ አላደርግም ማለቷን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
በተልዕኮው አሠራር እና የፋይናንስ መዋቅር ላይ ጉልህ ለውጦችን እንደምትሻም አስገንዝባለች ተብሏል።
በፈረንጆቹ ጥር 1 ሥራ የጀመረው አውሶም የቀድሞውን የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስ) ተክቷል። ከዚህ በፊት የነበሩት ተልዕኮዎች ከሶማሊያ ኃይሎች ጋር አሸባሪዎችን ሲዋጉ የነበረ ሲሆን አውሶም በብቸኝነት ስልጠና ላይ ያተኩራል። በዚህ ለውጥ ምክንያት አጠቃላይ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ በእጅጉ መቀነሱን ዘገባው ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X