አዲስ አበባ ቆሻሻን ጥቅም ላይ በማዋል ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበች
13:45 10.05.2025 (የተሻሻለ: 14:04 10.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ ቆሻሻን ጥቅም ላይ በማዋል ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበች
ገቢው ባለፉት ዘጠኝ ወራት እንደተገኘ የከተማዋ ጽዳት አስተዳዳር ኤጀንሲ አስታውቋል።
የመሥሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኘ ቆሻሻን ወደ ጠቃሚ ሀብት ለመቀየር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰፊ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ማሕበራት በሕጋዊ መንገድ እንዲደራጁ እና የድጎማ ስርዓት እንዲቋቋም መደረጉን ተከትሎ በቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ላይ ጉልህ ለውጥ ታይቷል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ334 በላይ ማሕበራት መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ተግባር የተሠማሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 53 የሚሆኑት የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማዘጋጀት ሥራ እንደሚሠሩ ተገልጿል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X