የብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎቶን ለግብርና ዘርፍ ልማት ሊጠቀሙ ይችላሉ ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎቶን ለግብርና ዘርፍ ልማት ሊጠቀሙ ይችላሉ ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታው ተናገሩ
የብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎቶን ለግብርና ዘርፍ ልማት ሊጠቀሙ ይችላሉ ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.05.2025
ሰብስክራይብ

የብሪክስ አባል ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎቶን ለግብርና ዘርፍ ልማት ሊጠቀሙ ይችላሉ ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታው ተናገሩ

ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ከሶስተኛው "ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰው ሰራሽ አስተለውሎት በግብርናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል ብለዋል።

“የብሪክስ ተነሳሽነት የአባል ሀገራቱን የተለያዩ ሀብቶች ይጠቀማል፡፡ ስለዚህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የግብርና ሃብቶችን እና የግብርና ምርቶችን ለማደራጀት እና ለመተንተን እንዲሁም ውጤቱን በመጠቀም ምርታማነትን ለመገመት ይረዳል" ብለዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የአምራች ኢንዱስትሪው በተለይ መልማት እንዳለበት ተቀምጧል ሲሉም ሚኒስትር ዲኤታው ጠቁመዋል።

“የአምራች ዘርፉን ዲጂታላይዝ ማድረግ አለብን፤ እንዲሁም የሰው ሃብትን ልናለማ ይገባል፡፡ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፖሊሲን በተመለከተ ሁለት አንኳር ነጥቦች አሉን። የመጀመሪያው ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ ለመጓዝ የሰው ኃይል ልማት ሲሆን ሌላው ደግሞ ኢንዱስትሪውን ለመለወጥ የሚደረግ ምርምርና ልማት ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0