ሴት ነጋዴዎች አብዛኛውን የኮሜሳ ክልል የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንደሚሸፍኑ የድርጅቱ ኃላፊ ተናገሩ
14:43 08.05.2025 (የተሻሻለ: 15:44 08.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሴት ነጋዴዎች አብዛኛውን የኮሜሳ ክልል የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንደሚሸፍኑ የድርጅቱ ኃላፊ ተናገሩ
የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቺካኩላ ሚቲ ሴቶች በአብዛኛው በግብርናው ዘርፍ እንደሚሠማሩ ከ6ኛው የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን የንግድ ትርዒት ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
"የኮሜሳ ክልል ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎችን ስንመለከት ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ናቸው፡፡ ሴቶች ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው" ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ሴቶች ሙሉ በሙሉ በንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ የሚያበረታታ ከባቢ ከተፈጠረላቸው ከዚህ የበለጠ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችሉ አንስተዋል።
"ሴቶች ካፒታል የሚቀርብላቸው ከሆነና በተሻለ መጠን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሁኔታዎች ከተመቻቹላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ የሚታየውን የካፒታል ማሸሽንም ይቀንሳል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X