ኢትዮጵያ መድኃኒት ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችል የወጪ ንግድ ምክር ቤት አቋቋመች
12:19 08.05.2025 (የተሻሻለ: 12:34 08.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ መድኃኒት ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችል የወጪ ንግድ ምክር ቤት አቋቋመች
የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾችን ጨምሮ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት አማካኝነት የተቋቋመው ምክር ቤት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን በተቀናጀ መልኩ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያሰበ ነው ተብሏል።
በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ 15 አዳዲስ ገበያዎችን በማዳረስ ዓመታዊ የወጪ ንግድን 20 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
በአሁኑ ጊዜ ከ260 በላይ መድኃኒቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 97 በመቶ የሚሆኑት ሀገር ውስጥ እንደሚመረቱ ተነግሯል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቀነባበረ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X