ፕሬዝዳንት ፑቲን ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

ሰብስክራይብ

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

ሩሲያ እና ቻይና በጋራ የታላቁን የአርበኝነት ጦርነት ታሪካዊ እውነት በማክበር የናዚነት መገለጫዎችን ይቃወማሉ።

የሩሲያ እና የቻይና ሕዝቦች የጦር ወንድማማችነት የሀገራቱ ግንኙነት መሠረት ነው።

ሩሲያ ለሺ ጂንፒንግ የሞስኮ ጉብኝት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች።

ሩሲያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩት ለሕዝቦቻቸው ጥቅም እንጂ ከሌሎች ሀገራት በተቃራኒ ለመቆም አይደለም።

የሩሲያ እና የቻይና መንግሥታት አጠቃላይ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እየሠሩ ነው።።

ፑቲን ሺ ጂንፒንግ በ80ኛው የድል በዓል ከሩሲያ ጋር ለመሆን በመወሰናቸው አመስግነው፤ በድጋሚ በቻይና ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት የጠቀሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦

ሺ ጂንፒንግ 80ኛውን የድል በዓል ምክንያት በማድረግ በበዓሉ ላይ በመገኘታቸው በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቻይና እና ሩሲያ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ታሪክ እውነታን ለማስጠበቅ ዝግጁ ናቸው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት ሰጥተዋል።

የሩሲያ እና የቻይና ሕዝቦች ከ80 ዓመታት በፊት ታላቁን ድል ለመቀዳጀት ከባድ ዋጋ በመክፈል በዓለም ሰላም እንዲሰፍን እና ለሰው ልጅ እድገት ትልቅ ታሪካዊ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0