አፍሪካውያን እርስ በርስ የሚያደርጉት ግብይት የአህጉሪቱን የንግድ አጀንዳ መሳካት ያረጋግጣል ሲሉ የቀደሞዋ የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ኃላፊ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካውያን እርስ በርስ የሚያደርጉት ግብይት የአህጉሪቱን የንግድ አጀንዳ መሳካት ያረጋግጣል ሲሉ የቀደሞዋ የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ኃላፊ ተናገሩ
አፍሪካውያን እርስ በርስ የሚያደርጉት ግብይት የአህጉሪቱን የንግድ አጀንዳ መሳካት ያረጋግጣል ሲሉ የቀደሞዋ የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ኃላፊ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.05.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን እርስ በርስ የሚያደርጉት ግብይት የአህጉሪቱን የንግድ አጀንዳ መሳካት ያረጋግጣል ሲሉ የቀደሞዋ የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች ፌዴሬሽን ኃላፊ ተናገሩ

የአህጉሪቱ ሴቶች ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሪዎች የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ሴቶችን ያማከሉ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ካትርሪን ኢቾያ ተናግረዋል።

“አፍሪካን ለማስተዋወቅ መሪዎቻችን የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ሴቶችን [ያማከሉ] መሆን አለባቸው፡፡ እነሱ የምርቶቻችን ምርጥ አስተዋዋቂዎች ናቸው፡፡ ሴቶቻችን የለበሷቸውን ልብሶች ተመልከት፤ ከዚህ የተሻለ ማግኘት አትችልም፡፡ ኢምፖርት ሳይሆን ኤክስፖርት ነው ልናደርግ የሚገባው" ሲሉ ከ6ኛው የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን የንግድ ትርዒት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አክለውም ሴቶች አሁን ባለው የኢኮኖሚ ስርዓት የሚጋጥሟቸውን ፈተናዎች ለመቅረፍ እንዲችሉ የፖሊሲ ለውጥ ያሻል ብለዋል፡፡

“የሴቶች ፖሊሲዎች ያስፈልጋሉ፡፡ በተለይም በግብርናው ዘርፍ...ቅድሚያ እንዲኖራቸውና ወደ ውጪ መላክ እንዲችሉ። ከዛ ባለፈ በኮሜሳ ቀጣና ውስጥ እርስ በርስ ልንገበያይ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የአፍሪካ የንግድ አጀንዳ መሳካቱን የምናረጋግጥበት አንደኛው መንገድ” ብለዋል፡፡  

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0