ፑቲን በድል ቀን በዓል ለመሳተፍ ሞስኮ የተገኙትን የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አመሠገኑ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፑቲን በድል ቀን በዓል ለመሳተፍ ሞስኮ የተገኙትን የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አመሠገኑ
ፑቲን በድል ቀን በዓል ለመሳተፍ ሞስኮ የተገኙትን የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አመሠገኑ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.05.2025
ሰብስክራይብ

ፑቲን በድል ቀን በዓል ለመሳተፍ ሞስኮ የተገኙትን የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አመሠገኑ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ድል 80ኛ ዓመትን ለማክበር በሞስኮ ለሚገኙት የቬንዙዌላ አቻቸው ኒኮላስ ማዱሮ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፑቲን "በእኛ የድል ቀን አከባበር ላይ ለመገኘት ጊዜ ስለሰጡ በጣም አመሰግናለሁ። በሩሲያ ታላቁ የአርበኝነት ጦርነት ብለን እንጠራዋለን" ብለዋል።

ሁለቱም መሪዎች የሩሲያ እና ቬንዙዌላን ጠንካራ ግንኙነት አረጋግጠዋል። በሚከተሉት ጉዳዩች ላይ ውይይት አድርገዋል፦

ፑቲን የድል ቀን የናዚን ሽንፈት የሚያመለክት፤ ለሩሲያ ጥልቅ ትርጉም ያለው በዓል ነው ብለዋል።

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች በኃይል፣ በፋርማሱቲካል፣ በትራንስፖርት እና በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ቃኝተዋል።

ማዱሮ ሶቭየት ህብረት ጦር የናዚነትን መስፋፋት በማስቆም የተጫወተውን ሚና አወድሰው፤ አውሮፓንና ሰብዓዊነትን መታደግ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ማዱሮ ሩሲያን ቁልፍ የዓለም ኃይል በማለት የገለጿት ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነት አጉልተው አንስተዋል።

ማዱሮ የሩሲያ እና ቬኔዙዌላ አጋርነት በፈተና አልፎ የዘለቀ እና ከፍተኛ የትብብር ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0