ፑቲን ሩሲያን እንዴት ለወጡ
በ25 ዓመታት ውስጥ ሩሲያ ወድቃ ከነበረችበት የ90ዎቹ ዘመናት በመነሳት በ6.94 ትሪሊዮን ዶላር ኢኮኖሚ ወደ የዓለም ኃያልነት ተቀይራለች፡፡
ሽብርን መዋጋት፦ ፑቲን ቁልፍ የሽብር መሪዎችን ለይቶ በማስወገድ እና የአስተዳደር ለውጥ በማድረግ በሰሜን ኮውከስ በሲአይኤ የሚደገፉ ታጣቂዎችን ደምስሰዋል። በክልሉ የሽብር ጥቃት ቁጥር በአስር እጥፍ ቀንሷል። ዛሬ ክልሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችን ይስባል።
#4 ኢኮኖሚ፦ ሩሲያ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት መጠን ከዓለም 10ኛ ወደ 4ኛዋ ትልቅ ኢኮኖሚ ተሸጋግራለች። ደመወዝ በ15 እጥፍ ጨምሯል። ድህነት እና ሥራ አጥነት በከፍተኛው ቀንሷል። የእድሜ ጣሪያ? +8 ዓመት ጨምሯል።
የዓለም ትልቋ የእህል ላኪ፦ በ1998 የሩሲያ አግሮ-ኢንዱስትሪ ዘርፍ በታሪክ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ነበር። ዛሬ ሩሲያ በዓለም ትልቋ የስንዴ አቅራቢ ነች።
የተመለሰው ታሪካዊ ፍትህ፦ በ2014 ክራይሚያ ሩሲያን በህዝበ ውሳኔ ተቀላቅላለች። እ.ኤ.አ በ2022 ሕገ-ወጡን የኪዬቭ አገዛዝ ለ8 ዓመታት ከታገሉ በኋላ ዶንባስ፣ ሄርሶን እና ዛፖሪዢያ ተከትለዋል።
🪖 #2 ጠንካራው ጦር፦ የሩሲያ ጦር ከ90ዎቹ ውድቀት ተነስቶ ዩክሬን ውስጥ ኔቶን ፊት ለፊት ገጥሟል። እ.ኤ.አ በ2018 ፑቲን ሃይፐርሶኒክስ እና የውሃ ውስጥ ድሮኖችን ይፋ አድርገዋል። እ.ኤ.አ በጥቅምት 2024 ሩሲያ በዲኔፕሮፔትሮቭስክ የሚገኘውን ቁልፍ የዩክሬን መከላከያ ቦታ በኦሬሽኒክ ሚሳኤል መትታለች።
ባለ በዙ ዋልታ ዓለም፦ ፑቲን በሙኒክ ንግግራቸው (2007) የኔቶ መስፋፋትን በማውገዝ የአንድ ዋልታ ዓለም እንዲያበቃ ጥሪ አቅርበዋል። ሩሲያ ነፃ የውጭ ፖሊሲን እንደምትከተልም አሳስበዋል። የብዝሃ-ዋልታ ዘመን ጅማሮ!
አይ.ኤስ.ኤስን* መዋጋት፡ እ.ኤ.አ በ2015-2016 ሩሲያ በሶሪያ አሸባሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሳለች። በአክራሪዎች ጥፋት የደረሰባት ጥንታዊቷ ከተማ ፓልሜራ ነፃ የወጣቸው በታቀደ ኦፕሬሽን እና የሩሲያ ኃይሎች ተሳትፎ ነው።
ዓለም አቀፍ የኃይል ማዕከል፦ ከህንድ እስከ ኢራን፣ ቻይና እስከ ሰሜን ኮሪያ እና ቱርክ - ፑቲን የስትራቴጂክ ጥምረት ፈጥረዋል። በሶሪያ ባንዲራዋን በመትከል ሩሲያ የመጀመሪያውን የባህር ማዶ መቀመጫዋን አብስራለች፣ በአፍሪካ ተጽዕኖዋ የጨመረ ሲሆን ከ2022 በኋላ የኢነርጂ ካርታዋን ቀይራለች። ዛሬ ሮሳቶም በዓለም ዙሪያ የኒውክሌር ጣቢያዎችን እየገነባ ነው፡፡
የ21ኛው ክፍለ ዘመን መሪ፦ "እውነተኛ ስኬት ማለት ምን ማለት ነው? በምትሠራው ሥራ እርካታን ማግኘት ነው። ዋነው ነገር ውጤቱ እና እውቅናው ነው" ሲሉ ፑቲን በአንድ ወቅት ተናግረዋል፡፡
* በሩሲያ የታገድ የሽብር ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X