እየተካረረ የመጣው የሕንድ እና ፓኪስታን ግጭት፤ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች?
10:38 07.05.2025 (የተሻሻለ: 10:54 07.05.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እየተካረረ የመጣው የሕንድ እና ፓኪስታን ግጭት፤ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች?
▪ ህንድ ኦፕሬሽን ሲንዶርን እንደጀመረች እና በፓኪስታን "የሽብርተኞች መሠረተ ልማቶች" በማለት በጠራቻቸው ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈፅማለች።
▪ኒው ዴልሂ የፓኪስታን ወታደራዊ ቦታዎች የጥቃቱ ዒላማ እንዳልሆኑ እና እርምጃዎቹ ውጥረቱን ለማባባስ የታሰቡ እንዳልሆኑ ገልፃለች።
▪ በምላሹ ፓኪስታን በህንድ ውስጥ ባሉ ዒላማዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰንዝራለች።
▪ፓኪስታን ህንድ በፈፀመችው ጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸውንና 35 ሰዎች መቁሰላቸውን አሳውቃለች። ኒው ዴልሂ በበኩሏ በድንበር ላይ የተኩስ ልውውጥ 3 ሰዎች መሞታቸውን ገልፃለች።
▪ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስላማባድ ህንድ ለፈጸመችው ጥቃት ጠንካራ ምላሽ የመስጠት ሙሉ መብት እንዳላት የገለፁ ሲሆን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱን "የጦርነት እወጃ" ሲል አውግዞታል።
▪ የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስትር ኒው ዴልሂ የምትታቀብ ከሆነ ኢስላማባድ ወታደራዊ እርምጃዎቿን ለማብረድ ዝግጁ ናት ሲሉ ከቆይታ በኋላ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X